Sidama Liberation Front

header hb
.


ማስታወሻ  ለተከበረ የኢፌዴሪ ጠቅላይ  ሚንስትር  ዶ/ር አብይ አህመድ

ይህ  የማሳሰቢያ  ጽሁፍ  የተላከዉ   ባለፉት ዘመናት በተፈራረቁት  የኢትዮጵያ  አገዛዞች  ሰር  እጅግ  አሰከፊ ግፍና በደል የደረሰበትና አሁንም  የባስ ብሎ  ከድጡ  ወደ ማጡ  ሆኖበት  የመጨረሻ ወድቀት   ጠርዝ  ላይ ደርሶ ካለዉ ከሲዳማ ህዝብ  ነዉ፡፡   

የተከበሩ የኢትዮጵያ መንግስት ጠቅላይ ሚንስትር  ዶ/ር አብይ  አህመድ  እርስዎ  ይንን  ከፍተኛ  የመንግስትና  የህዘብ አደራ  ያለበት  ሥልጣን ላይ መምጣትዎ እዉን  የመሆኑ  መልካም  ዜና  ከተሰማበት ሠዓት ጀምሮ  የሲዳማም  ህዝብ የወያኔ ሎሌ  ከበርቴ ካድሬዎች  ካጣሉበት  የባሪነትና የተገዥነት  ቀንበር ሰብሮ  ነጻ የወጣን  ያህል ደስታ ተስምቶታል፡፡ ምንም እንኳን ደስታዉን ለመግለጽ የሚያስችሉ መንገዶች ሁሉ የተዘጉበት ቢሆንም ፡፡  

ኢትዮጵያ ሀገራቸን  በወያኔ ኢህአዴግ  የጭቆና አገኣዝ ስር ከወቀደቀችበት  ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ  የኢትዮጵያን  ብሄር ብሄረሶቦችና ህዝቦችን  ድምጽ በማፈን  መነሻና መድረሻ በማይታወቅ  የፖለቲካ  መርከብ ላይ  አጭቆ  በጭፍን  በተጓዘበት ዐመታት ሁሉ  የጉዞ አቅጣጫ ልክ አይደልም ፤ ብንመካከር   ይሻላል፤  ይህ ጫወታ አላማረኝ  በአፍንጫዬ  በኩል  ደም የሸተኛል እንዳለችዉ አይጥ  ጥያቄዉን   የሚያነሱ  ብሄሮችንና ግለሰቦችን፤ጋጋዜኛችን  አንዱን  ጠባብ፣ ሌላዉን  የትምክህት ሃይሎች፤ አሸባሪዎች ፤ ጸረ- ልማቶች  ያለፈዉን  ስርዓት ናፋቂ  ወዘተ.. የሚል ታፔላ አየተለጠፈ መሪዉን   ብቻዉን ከተቀጣጠረዉ  መረከብ ላይ  አያራገፈ በዙዎችን  በነጻ እርምጃ እየገደለ ፤ እያሰረ፤ ወደ ዉጪ አገር  እንዲሰደዱ   ወይም የቁም እሰረኞች እዲሆኑ  ያሻዉን ሁሉ አደረገ፡፡

 ወያኔ ኢህአዴግ ዛሬ 27 ዓመት ላይ  የጉዞ አቅጣጫ  ጠፍቶበትና  መንገዱ  ጨልሞበት   መሪዉን  ጨርሶ በመተዉ ግራ ሲጋባ መርከቡ  አነሱንም  ጭምር ይዞ ገደል ሊገባና ተከስክሶ ሊበታተን የመጨረሻ ቋጥኝ ላይ ደርሶ    ሁሉም  ጣረ-ሞት ላይ  ባሉበት ሁኔታ  ዉስጥ  ፈጣሪ  ጣልቃ ገብቶ እርስዎን    የመርከቡን አቅጣጫ  በመቀየር   የኢትዮጵያ ህዘብ  ከሞትና ከጥፋት ለመታደግ  የሚያስችል  የመጨረሻ እድል  በእጅዎ  ዉስጥ እንዲገባ  አድርጎአል፡፡

ባለፉት አመታት  ያጋጠሙ  ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊና  ማህበራዊ   ቀዉሶች  አብዛኛዉን  ሆን ተብሎ  በእቅድና  በስልት  የተፈጸሙ በመሆኑ  የኢትየጵያን ብሄር፤ ብሄረሰቦችና ህዘቦችን   ወደ  ቀድሞዉ የተረጋጋ ማሀበራዊ ህይወት ለመመለስ  ጥበብና  ማስተዋል  በተሞላበት ሁኔታ  በፍጥነት  መገስገስ እንደሚያሰፈልግ  ይገነዘባሉ ብለን እናምናለን፡፡ለዚህም የፈጣሪ  ሞገስና ቸርነት እንዳይልይዎት ጸሎታችን ነዉ፡፡

ይህንን ከፍተኛ  አደራና  ሃላፊነት  በተረከቡበት መድረክ  ባደረጉት ንግግር  ዉስጥ  ከዚህ በፊት  እንደ ዳዊት ሲደገሙ የነበሩ  አድራሻ  የለሽ  አደናጋሪና አሰቀያሚ ቃላቶችና ህዝብ   የሚጸየፋቸዉ ቃላቶቸ (ጠባቦች፤ ትምክተኞች፤ ዐሸባሪዎች፤ ጸረ-ልማት ኃይሎች  የሚሉትን)  አለመጠቀምዎና  ይልቁንስ በተጻራሪዉ  ለቀድሞቹ እንደ እረት የሚመራቸዉን  ኢትዮጵያ አገራችን  የሚል ቃል  ከ20 ጊዜ  በላይ   ለመጠቀም  መፍቀደዎ እራሱ  መመርከቡን ከመስባበርና ከመስጠም  የመታደጊያ  የመጀመሪያ  ጥበብ ተደርጎ መዉስድ ይቻላል፡፡ ይህ ንግግር በሁሉም አቅጣጫ  የታወኩ ህዝቦች ለአፍታም ቢሆን  እንዲረጋጉ  አድርጎአል ለማለት ይቻላል፡፡ መልካም ንግግር ቁጣን ታበርዳለች ይል የለ ቃሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ   ያለ ወንጀላቸዉ  በወህኒ ሲማቅቁ ቆይተዉ  የተፈቱና  ከዘመድ አዝማድ ጋር  እንኳን ተፈታችሁ  ዝግጅት  አደረጋችሁ ተብሎ  ዳግም በግፍ የተሠሩ  ጋዜጠኖችና አምደኞች እንዲሁም  የአማራ ምሁራን  መፈታት  የእርሶዎ  ስልጣን አሻራዎች ናቸዉ  ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ  ወደ ምስራቅ የሀገሪቱ  ክፍል  ያደረጉት  ጉዞ በደም የተሳሰረዉንና  ለረጅም አመታት በጋራ ይኖሩ የነበረዉን  የኦሮሞና  የኢትዮጵያ  ሱማሌ  ህዘቦች  መካከል ጠላት የለኮሰዉ  ኢሳት ከሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች  ላይ ከፍተኛ  ሞትና  ስደት  አሰከትሎ የነበረዉ ዉጥረት እንዲረግብና  ቀደሞ ወደ ነበረበት ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችል  እርምጀ ለመዉሰድ  መሰረት የጣለ ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡

ወደ ትግራይም ሄደዉ ያደረጉት ዉይይትም  ስልጣንን ለምዝበራና  ለህዝቦች መጨቆኛ   ብቸኛ መንገድ  በማደድረግ  ስልጣን ላይ የመጡብናል ብለዉ የሚሰጉት  ወገኖች  ሌላዉን  ጭራቅ  እራሳቸዉን  ግን መላክ አስመስለዉ የሳሉ   ጭፍን አምባገነኖች የሰሩትን ኬላ የሰበረና ከፋፋዮችን  ባዶአቸዉን  በማስቀረት   የትግራይን ህዝብ  ከጥርጣረ   መንፈስ  እንዲወጣ  የረደ  ጉዳይ እንደሆነ ይታመናል፡፡

ወደ አማራ ክልል የተደረገዉ  ጉዞም  “የኦሮሞ  ሞት የአማራም ነዉ”በማለት  ባንድ  በኩል ጠባብና ጥምክህተኛ  የሚል ታፔላ እየተለጠፈባቸዉ  ተስማምተዉ ና  ተደራጅተዉ  ወደ ስልጣን  እንደይጠጉ  ለማሸማቀቅ  በሌላ በኩል ደግሞ እርስ በርስ እንዲጠራጠሩና   እንዲገፋፉ  ለማድረግ   የተበጀ ኬላን ያሰወገደና በሁለቱም ህዝቦች መካከል የበለጠ መተማመንን  እንደሚፈጥር  ጥርጥር የለዉም፡፡

በዚህ ሳምንት ደግሞ  ማለትም ሚያዝያ 18 ቀን 2010ዓ/ም  ወደ ደቡብ በማቅናት  በሀዋሳ ከተማ  የተለመደዉ ፋሽን  ተከትሎ በሚጋበዙ  የተለያዩ ህብረተ ሰብ ክፍሎች ጋር ይነጋገራሉ የሚል ወሬ በመላዉ ሲዳማ አከባቢ እየተናፈሰ ይገኛል፡፡

የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስተር  በዚህ ዉይይት ላይ የሲዳማን ህዝብ ቁልፍ  ፖለቲካዊ፤ አስተደደራዊና ኢኮኖሚያ  ጥያቄ ሊያነሱ የሚችሉ ግለሰቦች ፈጽሞ እንዳይገቡና  የሲዳማ ህዘብ ሰምም እንዳይነሳ  በደቡብ ከበርቴ ካድሬዎች  ልዩ  DNA ምርመራ በማድረግ  እንዲሳተፉ   በማድረግ የሀዋሳና የደቡብ ፖሊቲካ አልጋ ባልጋ እንደሆነና  ምንም  ጥያቄ  እንደለሌ   በማስመሰል የደኢህዴን ከበርቴ ካድሬዎች  በእርስዎ  ፊት  loyality achieve ለማድረግ ደፋ ቀና ማለት ጀምረዋል፡፡

ክብር ለሚገባዉ ክብር  መሰጠት  ተቀባይነት ያለዉ ቢሆንም አፌ ጨማዎች  ዉስጠ ወይራ  የወያኔ ቅጥር  የደቡብ ካድሬዎች  የሚናገሩትና የሚሰሩትን  ለማገናዘብ በጥበብ  ማጥናትን ይጠይቃል፡፡  ከፈጣሪዎቻቸዉና  ቀጣሪዎቻቸዉ ጋር  የገቡት  ህዝቦችን  ከፋፍሎና ጨቁኖ የመግዛት የጋራ ዉላቸዉ ገና ለወደፊት  ለረዥም አመታት ይቀጥላል ብለዉ ተስፋ  የሚያደርጉ አደርባይና  ደግሞም ህሊና ሳይሆን የሆድ ጉዳይ የሰበሰባቸዉ ስለሆነ በእርሶ ዘንድም  ተቀባይነት ላለማጣት ፈረንጆች እንደሚሉት  waging dogs  ባህሪይ  ተላብሰዉ ጭራቸዉን መቁላት ቢጀምሩ  ሊገረሙ አይገባም፡፡

ባጠቃላይ  አብዛኛዉ የደኢህዴን  ከበርቴ ካድሬዎች  ለጠቅላይ ሚንስትሩ  እዉነተኛ ፍቅርና ክብር ካላቸዉ   ጠቅላይ ሚንስትር ከአሮሞ ከሆነ አገር ይገነጥላሉና  ድምጽ በገንዘብ በመግዛት  ከደቡብ መመረጥ  አለበት የሚል ቅስቀሳ  በማድረግ ለምን እንቅልፍ አጥተዉ ከረሙ?  ለዚህም ተልዐኮና  

የተላላኪነት ሚና ለመወጣት ተብሎ ከ20,000,000 ብር በላይ ተሰብስቦአል  የሚል የአደባባይ ሩመር አለና  አግሬ መንገዳችንን  መጠቆም የምንፈልገዉ  በየሻይ ቤት እየዞሩ ከዜጎች አፍ የሚወጣዉን ቃላት  በመለቃቀም የሚተዳደሩ  ጆሮ ጠቢዎች  ይህ ወሬ ሳይደረሳቸዉ አይቀርምና የተላከዉን  ገንዘብ አነማን አዋጡት?እንደትሰ ተላከ?  የትስ ደረሰ?ምንስ  ተሰራበት? የሚሉትን ማጣራት ሳይጠቅም አይቀርም  እንላለን፡፡     

ወደ  ዋና የትኩረት ነጥብ  ስንመለስ

የሲዳማ ህዘብ ዘንድ  ከተማሪ አሰከተማሪ፤ ከገበሬ እሰከ ነጋዴ፤ከሊቅ አሰከ ደቂቅ  እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ከወዲሁ  ግንዛቤ አግኝተዉ  የሚጠበቅቦትን ከፍተኛ ሃላፊነት  በጥበብና  በጥንቃቄ  በመከታተል   አግባባነት ያለዉ   እርምጃ መዉስድ  እንዲችሉ  ይህ ማስታወሻ እንዲደርስዎ ተደርጎአል፡፡ ይህን  ማስተወሻ  እዉነተኛና  ሀቀኛ  ለሆኑ  የስራ አማካሪዎችዎ   ደርሶ  የራሳቸዉን  ሚና እንደጫወቱና  ተጨማሪ  ስልታዊ  ጥናት እንዲየደርጉና  የጉዳዩ   ተአማንነት  እንዲያጣሩ  በማድግ   በሲዳማና  አሮሞ ህዘቦች መካከል የተቀበረ ፈንጅ  ማምከኛ  ዘዴ ለመቀየስ ግማሽ መንገድ ሰለሚያሰጉዘን  በእጅጉ ሊተኮርበት ይገባል እንላለን፡፡

ለመሆኑ የሲደማ  ህዘብ ማነዉ? የመኖሪያ  ክልሉስ?

ከዚህ በፊት በአጼ ዘመን የሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት በሚባል  አስተዳደር፤ በደርግ ጊዜ  ደግሞ የሲዳሞ አስተዳደር  አከባቢ፤  በወያኔ ኢህአዴግ ለጥቂት ዓመታት በክልል ስምንትና  በመጨረሻም  የቀድሞ ሲዳሞ አስተዳደር አከባቢ፤ የጋሞ ጎፋ አስተዳደር፤ የከፋ አስተዳደር እና ከማአከላዊ ሸዋ አስተዳደር  ዉስጥ  ሀይቆችና ቡታጅራን  ጨምሮ  አንድ  ላይ  የታጭቀ  ፤ ለአስተዳደራዊ ምቹነት ሳይሆን  ለፖለቲካ ጫወታ  ታሳቢ ተደርጎ፤ ለሰፊዉ ህዝብ  ታስቦ ሳይሆን የደኢህዴን ቅጥር ካድሬዎች መፈንጫ ኢምፓየር  ወይም ነጻ  የወያኔ  ምሽግ  ለማዘጋጀት ታቅዶ  በተዋቀረዉ አርትፊሻል ከልል  ዉስጥ ታፍኖ ለመኖር የተወሰነበት ህዝብ ነዉ፡፡

የሲዳማ ህዝብ ቁጥር ስንት ነዉ

የደቡብ  ካድሬ  መንግሰት የሲዳማን ህዘብ ቁጥር  በትክክል  እንዲታወቅ  አይፈልጉም፡፡ የከልለሉ መንግሰት የሲዳማ  ህዘብ ቁጥር ነዉ  ብሎ የተቀበለዉና  ሌሎች  ኣለም አቀፍ   አጥኝዎች  የሚገልጹት በእጅጉ ይለያያል፡፡

 

ባጠቃለይ  የአሜረካ ስቴት ድፓርትመንት መረጃ መሰረት  በኢትዮጵያ  ከፍተኛዉን ቁጥር የሚይዝ የአሮሞ  ከኦሮሞ በመቀጠል አማራ  በሶስተኛ ደረጃ ሶስት ብሄሮችን ( ሲዳማ፣ ትግሬ እና የኢትየጵያ ሱማሌ) እንደሆነ ያሰቀምጣል፡፡ከዚህ አንጻር የሲዳማ  በኢትዮጵያ   ሶስተኛ ደረጃ  የሚይዝና በሀቅ ቢቆጠር   ከ6 ሚሊዮን በላይ  

የሆነ ህዝብ ነዉ፡፡ታዲያ ይህን ህዝብ ነዉ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት  ቅጥረኛ ካድሬዎቹ አማካይነት  ሰባአዊና ዲሞክራሳዊ  መብቶቹን  የሚያፍነዉ፡፡

የወታደራዊ ደርግ ስርዓትና ሲዳማ

በየዘመኑ በሚፈጠሩ  የነጻነት ጀግኖች  በግልና  በቡድን እየተደራጀ  የፊዉዳሉን  ስርዓት  የመታገል ልምድ  ቀጣይ ሆነ  የነጻነት ትግል ለማድረግና  ጨቋኙን  የደርግ  አገዛዝን በመቃወምና  በትጥቅ ትግል ለመፋለም በመወሰን አሰከ ሱማሌ  በረሀ  በእግር የወራት ጉዞ በማድረግ አራት ዙር  የወትድርና  ስልጠና በመዉስድና ወደ አገር ዉስጥ በመግባት  ባደረገዉ የጉሬላ ዉጊያ ከ1970 አሰከ 1975ዓ/ም ድረስ  ከደርግ  ጋር ባከሄደዉ ፍልሚያ/ጦርነት   ሀዋሳ  ከተማ ብቻ ሲቀር የሲዳሞን አስተዳደር  ሙሉ በሙሉ  የተቆጣጠረና  በ10 ሸህዎች የሚቀጠሩ የብሄሩ አባላትን   መስዋዕት ያደረገ  ለማንነቱና ለነጻነት  ቀናህ የሆነ ሀዘብ ነዉ፡፡

የወያኔ  ኢህአዴግ ቅጥር  የሆነ ደኢህዴን አገዛዝና የሲዳማ ህዝብ  

በ1983 ዓ/ም ወያኔ ኢትዮጵያን  ሲቆጣጠር የሲዳማ ህዘብ በደረግ ላይ ካለዉ ከፍተኛ ጥላቻ የተነሳ በጥርጣረም ቢሆን ለተወሰኑ ጥቅት ዓመታት ተቀበሎት ነበር፡፡ በ1985 ዓ/ም ከብሄሩ ስነ ልቦናና  ባህል ዉጭ በሆነ  ሁኔታ የሲዳማን ህዝብ ለማሸማቀቅ  ብሎ  ወደ አሮሬሳና ጭሪ ወረዳዎች  የተንቀሳቀሰዉ ስዉር ገዳይ ኃይል ህዝቡ  የለመደዉን የጀግንነት ምላሽ ከመስጠት ወደ ኋላ  እንደማይል  ስለተገነዘበ  አዘናግቶና  አለሳልሶ  በመቅረብ በ1985 ዓ.ም በሀሮሬሳ  ወረዳ  በምሽት እቤታቸው በሰላም በተኙበት ቤታቸዉ ሌሊት ከተገደሉ ጥቂቶቹ፤

አቶ  ሱንባሶ ሱሩራ፣ አቶ  ካንባታ የጤ ፣ አቶ ወላ ጎሶማ፣ አቶ  ሀጠሶ ጋማዳ፣ አቶ  ሄላ

ባናታ፣  አቶ  ማንሳ ሌዳሞ፣ አቶ በቀለ ላጊደ፣ አቶ መለሰ መንደፍሮ፣ አቶ ማቴ ማሻሻ፣ አቶ ጫሌ እና   በ1986 ዓ.ም በሆሮሬሳ ወረዳ ከቤታቸው ታፊነው ተወስደው በሀርቤጎና ወረዳ ሀፉርሳ በሚባል ጫካ ውስጥ እጃቸውን እንደታሰሩ በግፍ  ተረሽነው በጅምላ የተቀበሩ  ታጋዮች፡-ታጋይ ደምሴ ጋዊዋ፣ታጋይ ቱሚቻ ጋዊዋ፣ታጋይ ዶያሞ ድካ፣ታጋይ ድካ ጋንቡራና ታጋይ ሹጉራ ናማሮ ሲሆኑ  የግዲያው ዋናው ተዋናይና ስልት ቀያሽ  አቶ ሳሙኤል ሼባ ሲሆን ባሳየዉ የአስገዳይነትና  ፍጹም ቅጥርነቱ  ሚና  የእጅ መንሻ  የሆነዉ ዘንድ  የእድሜ ልክ ሹመቶች  እያገኘ የቆዬና በአሁኑ ጊዜም   የደኢህዴን ከፍተኛ ካድሬና የሲዳማ ዞን ፍትህና ጸጥታ መምሪያ  ኃላፊ ሆኖ  በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

አኚሁ አሰገዳይ ቅጥረኛ በቅርቡ በአሮሚያ አከባቢ የተነሳዉን ህዝባዊ አመጽ   ለመጨፍለቅ  ተብሎ  የወያኔ  ገዳይ ወታደሮችን  በሲዳማ ዞን በኩል  ወደ ምስራቃዊ  ባሌ  በሚስጥር  ተሰማርቶ ህዝቡን እንዲመታ የሚያስቸለዉን ስልት  ያቀነባበረና የመራ  ወታደርም  በድብቅ  አሳልፎ  እንዲሰፍር ያደረገ   ሰዉ ናቸዉ፡፡

ብዙሀን የተማሩ የሲዳማ ልጆች  ወደ ስልጣን  እንዳይቀርቡና  እንዲሰደዱ ተደርጎ  በአንደዚሁ ዓይነት  ትምህርት በሌላቸዉና ማንበብና መጸፍ ብቻ በሚችል ሰዉ እንዲተዳደር  በማድረግ ደኢህዴን በሲዳማ ህዝብ ላይ የግፍ ግፍ ይሰራበታል፡፡  

ሌላዉ  በሲዳማ ህዘብ  ላይ የተፈጸመዉ ዘግናኝ ና ጨካኝ  ህዝባዊ ጭፍጨፋ በግንቦት 16/1994 ዓ.ም (May 24, 2002 Sidama Loqe Massacre) በመባል በዓለም ደረጃ የተመዘገበ  የሀዋሳ-ሎቄ እልቂት   ሰላማዊና ንጹሀን የሲዳማ ልጆች በመንግስት ወታደሮች  የተጨፈጨፉበት ነዉ፡፡ የሲዳማ  አስተዳደር ከሀዋሳ እንዲወጣ ክልል የወሰነዉን  ለመቃወም ህገ መንግስት  በሚፈቅደዉ መሰረት  ሀሳቡን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለጽ  የሚስችለዉን ህጋዊ አካሄድ  ሲመክር ቆይቶ  ሰልፉን በሚያስተባብሩ ተወካዮች አማካይነት የሰልፉ  አላማ ለሲዳማ ዞን አስተዳደርና ለክልል  ቀርቦ የዞኑ  አስተዳደር ጥያቄዉን  አግባቢነት ተቀብሎ ሳለ የክልሉ መንግሰት  የሲዳማን ህዝብና ጥያቄ  በመናቅ  በፍጹም  አምባገነናዊ  መንገድ ምላሹን  ጥይት በማድረግ  በሰልፈኞቹ ላይ የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ በማድረጉ 65 ንጹሀን ሰዎች በአንድ ጀንበር ተጨፍጭፈዋል፡፡26 ንጹሃን ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ዝርዝር ሁኔታዉን የኢሰመጉ 51ኛ መግለጫዎች ቅጽ 2 ገጽ 284-291 መመልከት ይቻላል፡፡

የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ መብትና  ጥሰት

በኢትዮጵያ ህገ መንግስትና ይህንን መሰረት አድረጎ በወጠዉ  ስነስርዐት መሰረት የሲዳማ ህዝብ  የደቡብ ቅጥር  ከበርቴ ካድሬዎች ቀጥታና በተዘዋዋሪ የሚያደርሱበትን  ጭቆናና መሰሪ ጥፋት ለመገላገል  ህገ መንግስቱ በሚፈቅደዉ መሰረት ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር፤ ብሄረ-ሰብና ህዘብ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለዉ ይላልና ማንኛዉንም ህጋወዊ ስነ-ስርዓት በመጠበቅ የሲዳማ  ዞን ስር ያሉ የወረዳ ምክር ቤቶች ሙሉ በሙሉ በፍርማ አረጋግጠዉ  የማጠቃለያዉ  ዉሰኔ  በዞን ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ በፍርማ ተረጋግጦ  ለክልል  የቀረበ ጥያቄ  ህገ-መንገስታዊ ባልሆነ መንገድ  ባንድ አመት ዉስጥ በሲዳማ ዞን ዉስጥ ህዝቤ ዉሳኔ በማድረግና በማረጋገጥ ጥያቄዉን መመለስ የነበረበት  ደኢህዴን  ከፈዴራል ወየኔ ጋር  በመመሳጠር  በተለያዩ ሰበቦች  አስተጋጉሎእል፡፡

በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ᎂች ጠቅላይ ሚንስትር አቶ  መለስ  ዜናዊ ጠልቃ በመግባት  ጥቂት ቅጥር ካድሬዎችን በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ በመጋበዝ በማባበልና   በማጓጓት  ደግሞም  ጥቂት ሽማግሌዎችን   በመማጸን  በወቅቱ  ወያኔ ኢህአዴግን ከመንበረ ስልጣን ሊያስወግድ የሚቸል የተቃዋሚ  የኃይል ሚዛን ያየለበት  ወቅት መሆኑን  በመግለጽ  ለጥቂት  ወራት  ጊዜ እንዲታገሱት  ተማጸነዋል፡፡

ይሁን እንጂ  የካድሬን ሆድ በመሙላት ህገ-መንግስታዊ  የህዘብ ጥያቄ  ህገ- መንግስትን በጣሰ  መንገድ እስካሁን ድረስ እንደተጣሰ ይገኛል፡፡ የህዝብ ጥያቄ  ህዘብን በማይወክሉና  የህዘብን ጥያቄ ለራሳቸዉ ስልጣን  እርከን መወጣጫ  አድርገዉ  በሚንቀሳቀሱ  ጥቂት  የካድሬ ከበርቴዎች  አማካይነት ተጋርዶአል እነጂ  ህዝቡ ምላሹን አላገኘም፡፡ ከካድሬ ጋር  በመደራደርና የስልጣን ቀብድ በመስጠት ጣያቄዉን ወደ ጎን መተዉ በከፍተኛ ደረጃ የሲደማን ህዝብ መናቅ እንደሆነ ማሰገንዘብ  እንፈልጋለን፡፡

በሙታንና  ጥቂት የካድሬ ከበርቴዎች  የታፈነ የመብት ጥያቄ  ህያዉ  ሆኖ  በመጣዉ ጠቅላይ  ሚንስትር  ዶ/ር  አብይ አህመድ አማካይነት ተጨባጭ ምላሽ ይገኛል ብለን እናምናለን፡፡

የደቡብ ክልል የተዋቀረበት  ዋና   ዓለማ  ምንድ ነዉ?

የቀድሞ አራት  የአስተዳደር ክልሎቸንና  በወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመንም  ክልል 7፣ 8፤ 9 እና 10 የነበሩ ባንድ  ጀነበር ተጨፍለቀዉ  አንድ ክልል ሆናችኋል ተባለ፡፡ ግን ዓለማዉ  በፖለቲካዊና አስተዳደራዊ  መነጽር  በጥልቀት ከተመረመረ ሰምና ወርቅ ያለዉ  በርካታ  ዓለማዋች አሉት፡፡

ሰሙ፤  የደቡብ ብሄር ብሄረሶበችና  ህዘቦች አንድነት መሰረት ለመጣል፤ ልዩነታችን ወቤታችን  ከመፈክር ያላለፍ  የከበርቴ ካድሬዎች  ንግግር  ማደሚቀያና መደበቂያ ለማድረግ፡፡

ወርቁ ግን  1ኛ. የሲዳማ  የማንነትና የነጻነት ጥያቄ  ቀደምትነት ወያኔ በዉል ይረደዋልና  ወያኔም የትጥቅ  ትግሉን ለመቀጠል እንዲያመችዉ  ወደ ሶማሊያ  ባቀናበት  ወቅት ለወደፍትም  የትግል አጋር  ይሆናል በሚል ታሳቢ   የዚያድ በሬ አስተዳደርን  ቢሮ  እንዲከፍቱ  ያግባባለት  ከደርግ ጋር ለመፋለም  ሱማሊያ  የወትድርና ስልጠና  ጀምሮ የነበረዉ  ሲ.አ.ን  እንደሆነ  ያዉቃልና በአንድነት ሰበብ ከሁሉም የተሰበሰቡ ካድሬዎች  በሀዋሳ ከተማ መሽገዉ የሲዳማን ነጻነት ፈላጊዎች   እንቅስቃሴ  መቆጣጠር፤በሰበብ አስባቡ ማዳከምና  ስጋት  በማይፈጥር  ደረጃ  መደምስሰ ነዉ፡፡ ካድሬዎቹም  የተቀጠሩበት ዓለማ  አንዱ ይሀ ነዉና በርግጥም ይህ እቅድ ተሳክቶላቸዋል፡፡

የሲዳማ ነጻነት ታጋዮች በግፍ ተገለዋል፡፡  በርካታዎችም  መኖረያቸዉ  ወህኒ ሆኖአል፤ጥበበኞችና  አዋቂዎች ከአገር ተሰደዋል፡፡ በሲዳማ ህዘብ የተቋቋሙ የልማት ማሀበራትና  ተቋማት  ባሉበት እንዲቆሙ ወይም  ጉልህ ህዝባዊ ልማት ማካሄድ  ትተዉ  የካድሬ መጦሪያ  ሆነዉ እንዲያገለግሉ ተደርገዋል፡ወይም እንዲከስሙ ተፈርዶባቸዋል፡፡  

የሲዳማ ህዝብ ሰላማዊና  ማንንም የማገፋ ከሁሉም ብሄር ብሄረ ሰብ ጋር በፍቅር የኖረና እየኖረም ያለ መሆኑን ልቦናቸዉ እያወቀ  የካድሬ መንጋ በማሰማራት  ለሲዳማ ህዘብ የማይመጥን  የጠባብነት ታፔላ  በመለጠፍ  ማሸማቀቅ  ቂሚ  ስልታቸዉ ሆኖአል፡፡  

2ኛዉ ወርቁ የሲዳማን ህዘብ በተለያዩ ሰበብ  መሬቱን እየቀሙ ከሀዋሳ ከተማ አከባቢ   በመግፋት ቀስ በቀስ ከከተማ  እንዲረቁ በማድግና ቁጥሩን በመቀነስ፤ በምትኩም የእኛ ወገን  የሚሉትን  በመትከል  ማጆሪቲይ በማድረግ  ሲዳማ ዳግም በሀዋሳ ከተማ ላይ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥያቄ  የማያነሳበት ደረጃ ደርሶ ማኖሪቲይ እንደሆን  የማድረግ እቅድ ነዉ፡፡ይህንንም እቅድ  በተለያዩ ሰበባዊ  ፕቶጄክቶች ሰም በየዐመቱ በሺዎች  የመቆጠሩ አርሶ አደሮች እንዲፈናቀሉ አድርገዋል፡፡በሌላ በኩልም  ድብቅ ስልት   በመጠቀም የከተማ አስተዳደርን  በጥበብ በመቆጣጠር  አብዛኛዉ የቀበሌ የመንግስት ቤቶችንም  በዚህ አቅድ መሰረት  ወገናችን ለሚሉት  አስተላልፈዉ  የጨረሱ ስለሆነ  ከሲዳማ ብሄር ዉጪ የሆነ ህብረሰብ  ለመፍጠር  በጽናት ተንቀሳቅሰዉ  በተግባር አሳክተዋል፡፡

3ኛዉ   የወያኔን ድብቅ  ስልታዊ እቅድ ማሳካት ነዉ፡፡ ይሄዉም  ወያኔ ኢትዮጵያን ለመቶ ዐማታት ያለ ተቀናቃኝ ለመግዛት እንዲቻለዉ የአሮሞን  የማንነትና እራስን የማስተዳደር  ጥያቄ  ሁልጊዜም ቢሆን እንቅልፍ የነሰዋል፡፡ ስለዚህም  በጉልበት ለመቆጣጠር እንዲቻለዉ  ሳይጠሩት አቤት ሳይልኩት ወዴት የሚሉ ካድሬዎች የሚያስተዳደሩት  ከልል መፍጠር  ያስፈልገዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የደቡብ ካድሬ ምቹ  ሆነዉ ተገኙለት፡፡ ስለዚህ ከሀዋሳ ከተማን  ከሲዳማ  ብሄር በማጽዳት አከባቢዉን ጨምሮ ለፈዴራል ተጠሪ በማድረግ   የወታደር ምሽጉን በሀዋሳ ማእከልና በማስተዳደር የደቡብን  ህዘብ በአሮሞ ህዘብ ላይ አያዘመተ የመኖር ቅዠት  ተግባራዊ  ለማድረግ ነዉ፡፡ ለአብነት ያህል በቅርቡ የደቡብ ክልል ያወጣዉ የከተማ አስተዳደርና  ልማት አዋጅ  የዚህ  ድብቅ ሴራ አመልካች ነዉ፡፡ ይህንን ድበቅ አጀንዳ የያዘ አዋጅ  ተፈጸሚ ለማድረግ አንድም እርምጃ  ለመዉሰድ  መንቀሳቀስ ከፈተኛ ዋጋ  ያሰከፍላልና  እንዳይሞክሩት ብቻ ሳይሆን  እንዳያስቡት ልናስጠነቅቃቸዉ ይገባል፡፡  

4ኛና ዋነኛዉ  ደግሞ የሲዳማ ህዝብ በጉርብትና፤ በስነ-ልቦና  በባህል  በኢኮኖሚ ትስስር በተለይም  በዘር ግንዱ  ምክንያት  ድንገት  የደቡብን  ጭፍለቃ  ቀንበር ሰብሮ  ከኦሮሞ ህዘብ ጋር ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ  ግንኝት ከጀመረ  ደቡብ ክልል ይፈርሳልና  ለወያኔ አማራጭ  ነጻ  ምድር  ይጠፋል፡፡ስለዚህ በተቻለ መጠን በሁሉም  አቅጣጫ  የሲዳማን ህልዉና ማክሰምና  ከኦሮሞ ጋር  የመደራደርና የመቀራረብ ወኔና ጉልበት እንዳይኖር  ማድረግ ነዉ፡፡ ይህ ከፋፍለህ ግዛ መሴሪ ኬላ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሁለቱም ህዝቦች  ባህላዊ ትስስር ምክንያት በመሰበር ላይ ይገኛል፡፡ ለወፊትም በፍጥነት ኬላዉ ተሰባብሮ  የኦሮሞና የሲዳማ ህዝቦች አንድነት አደባባይ የሚወጣበት ጊዜ አጅግ ቅርብ  እንደሚሆን  ለጣላትም ለወዳጅም ይፋ ማድረግ  እንፈልጋለንል፡፡

ማጠቃለያ ሀሳብ

1ኛ.  የተከበሩ ጠቅላይ ሚንስትር  በሀዋሳ ከተማ  የሚሄዱት ወይይት ላይ ቅጥር ካድሬዎች እንጂ መላዉ የሲደማ  ሀሰብና ፍላጎት  የማይንጸባረቅበት  መሆኑን እንዲያዉቁልንና  በትክክል የሲዳማን ህዘብ የልብ ትርታ ሊሰሙ የሚችሉበት መድረክ ከቅጥር ካድሬ ንኪኪ  የጸዳ   ህዝባዊ ዉይይት መድረክ እነዲዘገጅ እንዲደረግልን

2ኛ. የከተሞች  ልማት ለማፋጠን በሚል ሰበብ  የሲዳማን ህዘብ  ከፖለቲካዉና ከአስተዳደራዊ መዋቅር       

 ወከልና በማሳጣት  ቀስ በቀስ የማጽዳት መሴሪ እቅድ ይዞ በፍጥነት ወደ ትግበራ እየተገባ ስለሆነ ሌላ ሰበብ ሳይከተል እንዲቆም እንዲደረግልን  ህዘባዊ ጥያቄያችንን እናቀርባል፡፡

Siddama Ejjeetto from Bansa Daayye